ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 55 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጥሪ ለተጠሙ

1. እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣ወደ ውሆች ኑ፤ኑና ግዙ፤ ብሉም፤ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።

2. ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ?በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጒልበታችሁን ትጨርሳላችሁ?ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።

3. ጆሮአችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ።ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ከእናንተም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

4. እነሆ፤ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፣መሪ፣ የጦር አዝማችም አድርጌዋለሁ።

5. እነሆ፤ የማታውቃቸውን መንግሥታት ትጠራለህ፤የማያወቁህ መንግሥታት በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ፤ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክህ፣የእስራኤል ቅዱስ፣በክብሩ ከፍ ከፍ አድርጎሃል።

6. እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ቀርቦም ሳለ ጥሩት።

7. ክፉ ሰው መንገዱን፣በደለኛም ሐሳቡን ይተው።ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

8. “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”ይላል እግዚአብሔር።

9. “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።

10. ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ምድርን በማራስ፣እንድታበቅልና እንድታፈራለዘሪው ዘር፣ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣

11. ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

12. በደስታ ትወጣላችሁ፤በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ተራሮችና ኰረብቶች፣በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ያጨበጭባሉ።

13. በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል።ይህም የእግዚአብሔር መታሰቢያ፣ሊጠፋ የማይችል፣የዘላለም ምልክት ይሆናል።”