ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በግብጽ ለሚደገፉ ወዮውላቸው

1. ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣በፈረሶች ለሚታመኑ፣በሠረገሎቻቸው ብዛት፣በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!

2. እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ቃሉን አያጥፍም።በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣በደለኞችንም በሚረዱ ላይ ይነሣል።

3. ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ተረጂውም ይወድቃል፤ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

4. እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦልየሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ብዙ እረኞችተጠራርተው ሲመጡበት፣ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።

5. በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”

6. እናንተ እስራኤላውያን ሆይ፤ እጅግ ወዳ መፃችሁበት ወደ እርሱ ተመለሱ።

7. በዚያን ቀን በኀጢአት የተሞላ እጃችሁ የሠራቸውን የወርቅና የብር ጣዖቶች ሁላችሁም ትጥላላችሁና።

8. “አሦር የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤የሥጋ ለባሽ ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል።ከሰይፍ ፊት ይሸሻል፤ጐልማሶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።

9. ጠንካራ ምሽጉ በሽብር ምክንያት ይወድቃል፤መሪዎቹም የጦር ዐርማ ሲያዩበድንጋጤ ይዋጣሉ”ይላል እሳቱ በጽዮን፣ማንደጃውም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።