ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከእሴይ ግንድ የወጣ ቍጥቋጥ

1. ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።

2. የእግዚአብሔር መንፈስ፣የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኀይል መንፈስ፣የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

3. እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።

4. ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።

5. ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።

6. ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፤ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሰባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።

7. ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ፤አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።

8. ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጒድጓድ ላይ ይጫወታል፤ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጒድጓድ ይከትታል።

9. በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ጒዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅትሞላለችና።

10. በዚያን ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።

11. በዚያን ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከታችኛው ግብፅ፣ ከላይኛው ግብፅ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

12. ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።

13. የኤፍሬም ምቀኝነት ያከትማል፤የይሁዳ ጠላቶችም ይቈረጣሉ፤ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።

14. በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።

15. እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣የግብፅን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎይለያየዋል፤ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።

16. እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜእንደሆነው ሁሉ፣ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።