ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከምድረ በዳው ማዶ ካለችው ከሴላ፣ለምድሪቱ ገዥ፣ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራየበግ ጠቦት ግብር ላኩ።

2. ከጐጆአቸው ተባርረውግራ እንደ ተጋቡ ወፎች፣የሞዓብ ሴቶችምበአርኖን ወንዝ መሻገሪያ እንዲሁ ይሆናሉ።

3. “ምክር ለግሱን፤ውሳኔ ስጡን፤በቀትር ጥላችሁንእንደ ሌሊት አጥሉብን፤የሸሹትን ደብቁ፤ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።

4. የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋር ይቈዩ፤እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።”የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ጥፋቱ ያከትማል፤እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።

5. ዙፋን በፍቅር ይመሠረታል፤ከዳዊት ቤት የሆነ፣በፍርድ ፍትሕን የሚሻ፣ጽድቅንም የሚያፋጥን፣አንድ ሰው በታማኝነት በላዩ ይቀመጣል።

6. የሞዓብን መዘባነን፣እጅግ መታበዩንና ኵራቱን፣እብሪቱንና ስድነቱን ሰምተናል፤ትምክህቱ ግን ከንቱ ነው።

7. ስለዚህ ሞዓባውያን ዋይ ይላሉ፤በአንድነትም ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማሉ፤ስለ ቂርሐራሴት ከተማ ሰዎች ትዝታ፣በሐዘን ያለቅሳሉ።

8. የሐሴቦን ዕርሻ፣የሴባማም የወይን ተክል ጠውልጎአል፤የአሕዛብ ገዦች፣ኢያዜርን ዐልፈው፣ምድረ በዳውን ዘልቀው፣ሥሮቻቸውን እስከ ባሕር ሰድደው የነበሩትንየተመረጡ የወይን ተክሎችንረጋግጠዋል።

9. ስለዚህ ስለ ሴባማ የወይን ተክል፣ኢያዜር እንዳለቀሰች፣ እኔም አለቅሳለሁ፤ሐሴቦን ሆይ፤ ኤልያሊ ሆይ፤በእንባዬ አርስሻለሁ፤ፍሬ ባፈራሽበት ወቅት የነበረው ሆታ፣መከርሽም ሲደርስ የነበረው ደስታ ተቋርጦአልና።

10. ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤እልልታም ቀርቶአል።በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና።

11. ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ በገና የሐዘን እንጒርጒሮ ታሰማለች፤አንጀቴም ስለ ቄርሔሬስ ታለቅሳለች፤

12. ሞዓብ ወደ ኰረብታዋ ብትወጣ፣ትርፏ ድካም ብቻ ነው፤ለጸሎት ወደ መቅደሷ ብትገባም፣ዋጋ የለውም።

13. እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ሞዓብ የተናገረው ቃል ይህ ነው።

14. አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የሞዓብ ክብርና የሕዝቧ ብዛት በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚቀረውም ሕዝብ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”