ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ስለ ኢየሩሳሌም የተነገረ ትንቢት

1. ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤እስቲ ምን ቢጨንቃችሁ ነው፤ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት?

2. አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤በጦርነትም አልሞቱም።

3. መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።

4. ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤አምርሬ ላልቅስበት፣ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።

5. እግዚአብሔር የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርበራእይ ሸለቆ፣የመጯጯኺያ የመረገጥና የሽብር፣ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።

6. ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ቂርም ጋሻዋን አነገበች

7. መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል፤

8. የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል።በዚያን ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤

9. የዳዊት ከተማ፣ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤በታችኛውም ኵሬ፣ውሃ አጠራቀማችሁ።

10. በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።

11. ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከ ታችሁም፤ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።

12. በዚያን ቀን ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣ጠጒራችሁን እንድትነጩማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።

13. ነገር ግን እነሆ፤ ተድላና ደስታ፣ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ፤“እንብላ እንጠጣነገ እንሞታለንና” አላችሁ።

14. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ገለጠልኝ፤ እንዲህም ሲል በጆሮዬ ሰማሁ፤ “ይህ ኀጢአት እስከምትሞቱበት ቀን ድረስ አይሰረይላችሁም” ይላል ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

15. ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሂድና ይህን መጋቢ፣የቤቱንም ኀላፊ ሳምናስን እንዲህ በለው፤

16. ‘እዚህ ምን ታደርጋለህ?በዚህ ስፍራ ለራስህ መቃብርን እንድ ታዘጋጅ፣በከፍታውም ላይ መቀበሪያህን እንድ ትወቅር፣ሬሳህ የሚያርፍበትንም ዐለት እንድ ትጠርብ ማን ፈቀደልህ?’

17. አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤ እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።

18. አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረበዚያ ትሞታለህ፤የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።

19. ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።

20. “በዚያን ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤

21. መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።

22. የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም።

23. በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ካስማ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል።

24. የቤተ ሰቡ ክብር፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም ከማሰሮ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል።

25. “በዚያ ቀን” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ “በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ ይነቀላል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።