ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የኢሳይያስ ተልእኮ

1. ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።

2. ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበሩ ነበር፤

3. እርስ በርሳቸው በመቀባበልም“ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለችቃ ይሉ ነበር።

4. ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

5. እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።

6. ከዚያም ከሱራፌል አንዱ፣ ከመሠዊያው ላይ የእሳት ፍም በጒጠት ወስዶ፣ ወደ እኔ እየበረረ መጣ።

7. አፌንም በእሳቱ ነክቶ፣ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኀጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለኝ።

8. ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት።እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” አልሁ።

9. እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤“ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።

10. የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ጆሮአቸውን ድፈን፤ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ይህ ካልሆነማ፣በዐይናቸው አይተው፣ በጆሮአቸው ሰምተው፣በልባቸውም አስተውለውበመመለስ ይፈወሳሉ።”

11. እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤“ከተሞች እስኪፈራርሱና፣የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፣ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤

12. እግዚአብሔርም ሰዎችን እስከሚያርቅ፣ምድሪቱም ጨርሶ ባዶ እስክትሆን፣

13. ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠጊዜ ጒቶ እንደሚቀር፣ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጒቶ ሆኖ ይቀራል።”