ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት

1. ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች።የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።

2. ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ራስ ሁሉ ተመድምዶአል፤ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል።

3. በየመንገዱም ማቅ ይለብሳሉ፤በየሰገነቱና በየአደባባዩሁሉም ያለቅሳሉ፤እንባም ይራጫሉ።

4. ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ድምፃቸው እስከ ያሀድ ድረስ ተሰማ፤ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ልባቸውም ራደ።

5. ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤እንባቸውን እያፈሰሱወደ ሉሒት ወጡ፤በሖሮናይም መንገድም፣ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።

6. የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤ሣሩ ጠውልጎአል፤ቡቃያውም ጠፍቶአል፤ለምለም ነገር አይታይም።

7. ስለዚህ ያገኙትን ሀብት፣ያከማቹትን ንብረት ከአኻያ ወንዝ ማዶ ተሸክመው ያሻግሩታል።

8. ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣ሰቈቃቸውም እስከ ብኤርኢሊም ደረሰ።