ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 59 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኀጢአት፣ ንስሓና መበዤት

1. እነሆ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፤ጆሮውም መስማት አልተሳናትም

2. ነገር ግን በደላችሁከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤በዚህም ምክንያት አይሰማም።

3. እጆቻችሁ በደም፣ጣቶቻችሁ በበደል ተነክረዋል፤ከንፈሮቻችሁ ሐሰትን ተናገሩ፤ምላሶቻችሁ ክፉ ነገርን አሰሙ።

4. ፍትሕን የሚጠራ ማንም የለም፤ጒዳዩን በቅንነት የሚያቀርብ የለም፤በከንቱ ነገር ታመኑ፤ ሐሰትን ተናገሩ፤ሁከትን ፀነሱ፤ ክፋትንም ወለዱ።

5. የእባብ ዕንቍላል ታቀፉ፤የሸረሪት ድር አደሩ፤ዕንቍላሎቻቸውን የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤አንዱ በተሰበረ ጊዜም እፉኝት ይወጣል።

6. ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑም፤በሚሠሩትም ሰውነታቸውን መሸፈን አይችሉም፤ሥራቸው ክፉ ነው፤እጃቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞላ ነው።

7. እግሮቻቸው ወደ ኀጢአት ይሮጣሉ፤ንጹሕ ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤የሚያስቡት ክፉ ሐሳብ ነው፤ማጥፋትና ማፈራረስም የመንገዳቸው ምልክት ነው።

8. የሰላምን መንገድ አያውቁም፤በጐዳናቸውም ፍትሕ የለም፤መንገዳቸውን ጠማማ አድርገውታል፤በዚያም የሚሄድ ሰላም አያገኝም።

9. ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ጽድቅም ወደ እኛ አይመጣም፤ብርሃንን ፈለግን፤ ነገር ግን ሁሉ ጨለማ ነው፤የብርሃንን ጸዳል ፈለግን፤ የምንሄደው ግን በድንግዝግዝታ ነው።

10. በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ጀምበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን።

11. ሁላችን እንደ ድቦች እናላዝናለን፤እንደ ርግቦችም በመቃተት እንጮኻለን፤ፍትሕን ፈለግን፤ ግን አላገኘንም፤ትድግናን ፈለግን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቆአል።

12. በደላችን በፊትህ በዝቶአል፤ኀጢአታችን መስክሮብናል፤በደላችን ከእኛ አልተለየም፤ዐመፀኝነታችንንም እናውቃለን።

13. በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።

14. ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ጽድቅም በሩቁ ቆሞአል፤እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሎአል፤ቅንነትም መግባት አልቻለም።

15. እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ።

16. ማንም እንደሌለ አየ፤ወደ እርሱ የሚማልድ ባለመኖሩ ተገረመ፤ስለዚህ የገዛ ክንዱ ድነት አመጣለት፤የራሱም ጽድቅ ደግፎ ያዘው።

17. ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤የድነትን ቊር በራሱ ላይ ደፋ፤የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ።

18. እንደ ሥራቸው መጠን፣ቊጣን ለባላጋራዎቹ፣ፍዳን ለጠላቶቹ፣እንደዚሁ ይከፍላቸዋል፤ለደሴቶችም የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።

19. በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና።

20. “አዳኝ ወደ ጽዮን፣ኀጢአታቸውንም ወደ ተናዘዙት ወደ ያዕቆብ ቤት ይመጣል”ይላል እግዚአብሔር።

21. “በእኔ በኩል፣ ከእነርሱ ጋር ያለኝ ቃል ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “በአንተም ላይ ያለው መንፈሴ፣ በአፍህ ያስቀመጥሁት ቃሌ ከአፍህ፣ ከልጆችህ አፍ፣ ከዘር ዘሮቻቸውም አፍ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም አይለይም” ይላል እግዚአብሔር።