ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 64 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አቤቱ፤ ሰማያትን ቀድደህ ምነው በወረድምነዋ ተራሮች በፊትህ በተናወጡ

2. እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ውሃንም እንደሚያፈላ፣ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ።

3. እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።

4. ከጥንት ጀምሮ፣በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም።

5. በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣እነሆ፣ ተቈጣህ፤ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?

6. ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።

7. ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።

8. ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤

9. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።

10. የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆኑ፤ጽዮን ራሷ እንኳ ምድረ በዳ፣ ኢየሩሳሌምም የተፈታች ሆናለች።

11. አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣በእሳት ተቃጥሎአል፤ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ አትመለስምን?ዝም ብለህ ከልክ በላይ ትቀጣናለህን?