ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእስራኤል ዐርነት መውጣት

1. በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንንበብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።

2. በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤“ለመልካሙ የወይን ቦታ ዘምሩለት፤

3. እኔ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ዘወትር ውሃ አጠጣዋለሁ፤ስለዚህ ማንም አይጐዳውም፣ቀንና ሌሊት እጠብቀዋለሁ፤

4. እኔ አልቈጣም።እሾኽና ኵርንችት ምነው በተነሡብኝ!ለውጊያ በወጣሁባቸው፣አንድ ላይ ባቃጠልኋቸው!

5. አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠሩ፤አዎን፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።”

6. በሚመጡት ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤እስራኤልም ያቈጠቍጣል፤ ያብባልም፤በፍሬያቸውም ምድርን ሁሉ ይሞላሉ።

7. የመቷትን እንደ መታቸው፣ እግዚአብሔር እርሷንስ መታትን?የገደሏትን እንደ ገደላቸው፣እርሷስ ተገደለችን?

8. በጦርነትና በስደት ተፋለምሃት፤የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን፣በብርቱ ዐውሎ ነፋስ አሳደድሃት።

9. ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቃቸው፣የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣በዚያን ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ይህም ኀጢአቱን የማስወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።

10. የተመሸገባት ከተማ ባዶዋን ቀርታለች፤እንደ ምድረ በዳም የተተወች ስፍራ ሆናለች፤ጥጆች በዚያ ይሰማራሉ፤እዚያም ይተኛሉ፤ቅርንጫፎቿንም ልጠው ይበላሉ።

11. ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል።ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ፈጣሪው አይራራለትም፤ያበጀውም አይምረውም።

12. በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ፤ እግዚአብሔር እህሉን ይወቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።

13. በዚያ ቀን ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር የጠፉትና በግብፅ የተሰደዱትም መጥተው፣ በተቀደሰው ተራራ በኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን ያመልካሉ።