ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40
  41. 41
  42. 42
  43. 43
  44. 44
  45. 45
  46. 46
  47. 47
  48. 48
  49. 49
  50. 50
  51. 51
  52. 52
  53. 53
  54. 54
  55. 55
  56. 56
  57. 57
  58. 58
  59. 59
  60. 60
  61. 61
  62. 62
  63. 63
  64. 64
  65. 65
  66. 66

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእግዚአብሔር አገልጋይ

1. “ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣በእርሱም ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።

2. አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም።

3. የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።

4. ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”

5. ሰማያትን የፈጠረ፣ የዘረጋቸውም፣ምድርንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ያበጀ፣ለሕዝቧ እስትንፋስን፣ለሚኖሩባትም ሕይወትን የሚሰጥ፣ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

6. “እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤እጅህንም እይዛለሁ፤እጠብቅሃለሁ፤ለሕዝቡ ቃል ኪዳን፣ለአሕዛብም ብርሃን አደርግሃለሁ።

7. የዕውሮችን ዐይን ትከፍታለህ፤ምርኮኞችን ከእስር ቤት፣በጨለማ የተቀመጡትንም ከወህኒ ታወጣለህ።

8. “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው፤ክብሬን ለሌላ፣ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም።

9. እነሆ፤ የቀድሞው ነገር ተፈጽሞአል፤እኔም አዲስ ነገር እናገራለሁ፤ከመብቀሉም በፊት፣ለእናንተ አስታውቃለሁ።

ለእግዚአብሔር የውዳሴ መዝሙር

10. እናንት ወደ ባሕር የምትወርዱ፣ በዚያም ያላችሁ ሁሉ፣ደሴቶችና በዚያ የምትኖሩ በሙሉ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ከምድር ዳርቻም ምስጋናውን ዘምሩ።

11. ምድረ በዳውና ከተሞቹ ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ቄዳር ያለችበት መንደር ደስ ይበለው፤የሴላ ሕዝቦች በደስታ ይዘምሩ፤ከተራሮችም ራስ ላይ ይጩኹ።

12. ክብር ለእግዚአብሔር ይስጡ፤ምስጋናውንም በደሴቶች ያውጁ።

13. እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤እንደ ተዋጊ በወኔ ይነሣል፤የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።

14. “ለረጅም ጊዜ ዝም አልሁ፤ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣እጮኻለሁ፤ ቁና ቁና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።

15. ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ኵሬውን አደርቃለሁ።

16. ዕውሮችን በማያወቁት መንገድእመራቸዋለሁ፤ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ።ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ።ይህን አደርጋለሁ፤አልተዋቸውም።

17. በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።

ዕውሯና ደንቈሮዋ እስራኤል

18. “እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።

19. አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ?ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ?ለእኔ ታማኝ እንደሆነ ሰው የታወረ፣እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው?

20. ብዙ ነገርን አያችሁ፤ ነገር ግን አላስተዋላችሁም፤ጆሮአችሁ ክፍት ነው፤ ነገር ግን ምንም አትሰሙም።”

21. እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሲል፣ሕጉን ታላቅና የተከበረ በማድረግ ደስአለው።

22. ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣በጒድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ተበዝብዘዋል፣የሚያድናቸውም የለም፤ተማርከዋል፣“መልሷቸው” የሚልም የለም።

23. ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው?

24. ያዕቆብን ለዝርፊያ፣እስራኤልን ለምርኮ የዳረገ ማነው?በኀጢአት የበደልነው፣ እግዚአብሔር አይደለምን?መንገዱን ለመከተል፣ለሕጉም መታዘዝ አልፈለጉምና።

25. ስለዚህ የሚነድ ቍጣውን፣የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።