ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤል በሮብዓም ላይ ዐመፀ

1. እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደዚያ ሄደው ሰለነበር፣ ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።

2. ከንጉሥ ሰሎሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ሲሰማ፣ ከግብፅ ተመልሶ መጣ።

3. እርሱንም ልከው አስጠሩት፤ ከዚያም እርሱና እስራኤል ሁሉ ወደ ሮብዓም ሄደው እንዲህ አሉት፤

4. “አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”

5. ሮብዓምም፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ።

6. ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም፣ “ለዚህ ሕዝብ ምን እንድመልስለት ትመክሩኛላችሁ?” በማለት አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ ያገለገሉትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠየቃቸው።

7. እነርሱም፣ “ለእዚህ ሕዝብ ደግ ከሆንህለት፣ ደስ ካሰኘኸውና የሚስማማው መልስ ከሰጠኸው ምንጊዜም ይገዛልሃል” አሉት።

8. ሮብዓም ግን ሽማግሌዎች የሰጡትን ምክር ትቶ፣ አብሮ አደጎቹና አገልጋዮቹ ከሆኑት ወጣቶች ምክር ጠየቀ፤

9. እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድ ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?”

10. አብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ለጠየቊህ ሕዝብ፤ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤

11. አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።”

12. ንጉሡ፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ሮብዓም ተመለሱ።

13. ንጉሡም የሽማግሌዎችን ምክር በመናቅ፣ አመናጭቆ መለሰላቸው፤

14. እርሱም የወጣቶቹን ምክር በመቀበል፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።

15. እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ወስኖ ስለ ነበር፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።

16. መላው እስራኤልም ንጉሡ ሊሰማቸው አለመፈለጉን በተረዱ ጊዜ፣ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤“ከዳዊት ምን ድርሻ አለን?ከእሴይስ ልጅ ምን ክፍል አለን?እስራኤል፣ ሆይ፤ ወደ ድንኳንህ ተመለስ፤ዳዊት ሆይ፤ አንተም የገዛ ቤትህን ጠብቅ።”ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ የቤታቸው ተመለሱ።

17. ይሁን እንጂ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩትን እስራኤላውያን አሁንም የሚገዛቸው ሮብዓም ነበር።

18. ንጉሥ ሮብዓም የገባሮች ኀላፊ የነበረውን አዶራምን ላከው፤ እስራኤላውያን ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደምንም ብሎ ሰረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሽቶ አመለጠ።

19. ስለዚህ እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንደ ዐመፀ ነው።