ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነገ በሚሆነው አትመካ፤ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና።

2. ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን።

3. ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የተላላ ሰው ጒነጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።

4. ንዴት ጨካኝ፣ ቊጣም ጐርፍ ነው፤በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?

5. የተገለጠ ዘለፋ፣ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።

6. ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣የወዳጅ ማቊሰል ይታመናል።

7. ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።

8. ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።

9. ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።

10. የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

11. ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው፤ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።

12. ጥንቁቅ አደጋን አይቶ ይሸሸጋል፤ማስተዋል የጐደለው ግን ወደዚያው ይሄዳል፤ ይጐዳልም።

13. ለማይታወቅ ሰው የተዋሰን ልብሱን ግፈፈው፤ለዘልዛላ ሴት ከተዋሰማ አግተው።

14. ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣እንደ ርግማን ይቈጠራል።

15. ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥጠፈጠፍ ናት፤

16. እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትንበእጅ እንደ መጨበጥ ነው።

17. ብረት ብረትን እንደሚስል፣ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።

18. በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።

19. ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጦ ያሳያል።

20. ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣የሰውም ዐይን አይረካም።

21. ብር በማቅለጫ፣ ወርቅ በከውር እንደሚፈተን፣ሰውም በሚቀበለው ምስጋና ይፈተናል።

22. ጅልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቀው፣ጅልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።

23. በጎችህ በምን ሁኔታ እንዳሉ ደህና አድርገህ ዕወቅ፤መንጋህንም ተንከባከብ፤

24. ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም።

25. ደረቁ ሣር ተወግዶ፣ አዲሱ ብቅ ሲል፣በየኰረብታው ላይ ያለው ሣር ተሰብስቦ ሲገባ፣

26. ከበግ ጠቦቶች ልብስ ታገኛለህ፤ፍየሎችም የዕርሻ መሬት መግዣ ይሆኑሃል።