ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጠቢብ ልጅ የአባቱን ምክር በማስተዋል ይሰማል፤ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አያዳምጥም።

2. ሰው ከከንፈሩ ፍሬ መልካም ነገር ያገኛል፤ወስላቶች ግን ዐመፅን ይናፍቃሉ።

3. አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።

4. ሰነፍ አጥብቆ ይመኛል፤ አንዳችም አያገኝም፤የትጉዎች ምኞት ግን ይረካል።

5. ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል።

6. ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች።

7. ምንም ሳይኖረው ባለጠጋ መስሎ የሚታይ ሰው አለ፤ሌላው ድኻ መስሎ ይታያል፤ ግን ብዙ ሀብት አለው።

8. የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

9. የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።

10. ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።

11. ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።

12. ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።

13. ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል።

14. የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ሰውን በሞት ወጥመድ እንዳይያዝ ታደርገዋለች።

15. መልካም ማስተዋል ሞገስን ታስገኛለች፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው።

16. አስተዋይ ሰው ሥራውን በዕውቀት ያከናውናል፤ተላላ ግን ሞኝነቱን ይገልጣል።

17. ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፤ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስን ያመጣል።

18. ተግሣጽን የሚንቅ ወደ ድኽነትና ኀፍረት ይሄዳል፤ዕርምትን የሚቀበል ሁሉ ግን ይከበራል።

19. ምኞት ስትፈጸም ነፍስን ደስ ታሰኛለች፤ተላሎች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።

20. ከጠቢብ ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤የተላሎች ባልንጀራ ግን ጒዳት ያገኘዋል።

21. መጥፎ ዕድል ኀጢአተኛን ይከታተላል፤ብልጽግና ግን የጻድቃን ዋጋ ነው።

22. ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።

23. የድኾች ዕርሻ የተትረፈረፈ ምርት ያስገኛል፤የፍትሕ መጓደል ግን ጠራርጎ ይወስደዋል።

24. በአርጩሜ ከመቅጣት የሚሳሳለት ልጁን ይጠላል፤የሚወደው ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።