ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሰኘዋል።

2. ትዕቢት ስትመጣ ውርደትም ትከተላለች፤በትሑት ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።

3. ቅኖችን ትክክለኛነታቸው ትመራቸዋለች፤ወስላቶች ግን በገዛ አታላይነታቸው ይጠፋሉ።

4. በቊጣ ቀን ሀብት ፋይዳ የለውም፤ጽድቅ ግን ከሞት ትታደጋለች።

5. ለፍጹማን ሰዎች ጽድቃቸው መንገዳቸውን ታቃናላቸዋለች፤ክፉዎች ግን በገዛ ክፋታቸው ይወድቃሉ።

6. ቅኖችን ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፤ወስላቶች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ።

7. ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ከንቱ ትሆናለች፤በኀይሉ የተመካበትም ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል።

8. ጻድቅ ከመከራ ይድናል፤ይልቁን መከራው በክፉው ላይ ይደርሳል።

9. ክፉ ሰው ባልንጀራውን በአፉ ያጠፋል፤ጻድቃን ግን በዕውቀት ያመልጣሉ።

10. ጻድቃን ሲሳካላቸው ከተማ ደስ ይላታል፤ክፉዎች ሲጠፉ እልልታ ይሆናል።

11. በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤በክፉዎች አንደበት ግን ትጠፋለች።

12. ማመዛዘን የጐደለው ሰው ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል።

13. ሐሜተኛ ምስጢር አይጠብቅም፤ታማኝ ሰው ግን ምስጢር ይጠብቃል።

14. በአመራር ጒድለት መንግሥት ይወድቃል፤የመካሮች ብዛት ግን ድልን ርግጠኛ ያደርጋል።

15. ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራ ያገኘዋል፤ዋስትና ለመስጠት እጅ የማይመታ ግን ምንም አይደርስበትም።

16. ርኅሩኅ ሴት ክብር ታገኛለች፤ጒልበተኛ ሰዎች ግን ብልጽግናን ብቻ ያገኛሉ።

17. ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል።

18. ክፉ ሰው የሚያገኘው ትርፍ መቅኖ የለውም፤ጽድቅን የሚዘራ ግን አስተማማኝ ዋጋ ያገኛል።

19. እውነተኛ ጻድቅ ሕይወትን ያገኛል፤ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞቱ ይጓዛል።

20. እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል።

21. ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።

22. በእርያ አፍንጫ ላይ እንደ ተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ማስተዋል የጐደላት ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት።

23. የጻድቃን ምኞት ምንጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤የክፉዎች ተስፋ ግን በቊጣ ያከትማል።

24. አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል።

25. ለጋስ ይበለጽጋል፤ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።

26. በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል።

27. በጎ ነገርን ተግቶ የሚሻ በጎ ነገር ይጠብቀዋል፤ክፉ ነገር የሚፈልገውን ግን ክፉ ያገኘዋል።

28. በሀብቱ የሚታመን ሁሉ ይወድቃል፤ጻድቃን ግን እንደ አረንጓዴ ቅጠል ይለመልማሉ።

29. ቤተ ሰቡን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ተላላም ሰው የጠቢብ ሎሌ ይሆናል።

30. የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፤ነፍሳትን የሚማርክም ጠቢብ ነው።