ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጥበብ ከሁሉ በላይ መሆኗ

1. ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።

2. በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ።

3. በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣

4. አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤“ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።

5. ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤ቃሌን አትርሳ፤ ከእርሷም ዘወር አትበል።

6. ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች።

7. ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።

8. ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤

9. በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።

10. ልጄ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ቃሌንም ልብ በል፤የሕይወት ዘመንህም ትበዛለች።

11. በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ።

12. ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ስትሮጥም አትደናቀፍም።

13. ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።

14. ወደ ኀጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤

15. ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤

16. ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ ባይናቸው አይዞርም።

17. የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

18. የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።

19. የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።

20. ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።

21. ከእይታህ አታርቀው፤በልብህም ጠብቀው፤

22. ለሚያገኘው ሕይወት፤ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።

23. ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤የሕይወት ምንጭ ነውና።

24. ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ።

25. ዐይኖችህ በቀጥታ ይመልከቱ፤ትክ ብለህም ፊት ለፊት እይ።

26. የእግርህን ጐዳና አስተካክል፤የጸናውን መንገድ ብቻ ያዝ።

27. ወደ ቀኝ ወደ ግራ አትበል፤እግርህን ከክፉ ጠብቅ።