ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእስራኤል ወንዶች ልጆች

1. የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣

2. ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር።

ይሁዳ

እስከ ኤስሮን ወንዶች ልጆች

3. የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።

4. የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።

5. የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ኤስሮም፣ ሐሙል።

6. የዛራ ወንዶች ልጆች፤ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፤ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።

7. የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤እርሱም ፈጽሞ መደምሰስ የነበረበትን ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።

8. የኤታን ወንድ ልጅ፤አዛርያ።

9. የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።

ከኤስሮም ልጅ ከአራም ጀምሮ ያለው የትውልድ ሐረግ

10. አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤

11. ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።

12. ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ።

13. የእሴይ ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣

14. አራተኛ ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣

15. ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።

16. እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።

17. አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።

የኤስሮም ልጅ ካሌብ

18. የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ ከዓዙባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ያሳር፣ ሶባብ፣ አርዶን።

19. ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።

20. ሆር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።

21. ከዚያም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።

22. ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።

23. ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ሥልሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።

24. ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።

የኤስሮም ልጅ ይረሕምኤል

25. የኤስሮም የበኵር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም፣ አኪያ።

26. ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናምን እናት ነበረች።

27. የይረሕምኤል የበኵር ልጁ የራም ወንዶች፤መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።

28. የኦናም ወንዶች ልጆች፤ሸማይና ያዳ።የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ናዳብና አቢሱር።

29. የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።

30. የናባድ ወንዶች ልጆች፤ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።

31. የአፋይም ወንድ ልጅ፤ይሽዒ። ይሽዒም ሶሳን ወለደ።ሶሳን አሕላይን ወለደ።

32. የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።

33. የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ፌሌት፣ ዛዛ።እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።

34. ሶሳን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው።

35. ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓታይ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።

36. ዓታይ ናታንን ወለደ፤ናታንም ዛባድን ወለደ፤

37. ዛባድ ኤፍላልን ወለደ፤ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤

38. ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤

39. ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ኬሌስ ኤልዓሣን ወለደ፤

40. ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤

41. ሰሎም የቃምያን ወለደ፤የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።

የካሌብ ጐሣዎች

42. የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።

43. የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ቆሬ፣ ተፉዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።

44. ሽማዕ ረሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሸማይን ወለደ፤

45. ሸማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።

46. የካሌብ ቁባት ዔፉ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።

47. የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።

48. የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደችለት።

49. እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።

50. እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ።የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ሦባል የቂርያትይዓሪም አባት፤

51. ሰልሞን የቤተ ልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።

52. የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኵሌታ፣ ሀሮኤ፤

53. እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጐሣዎች፤ ይትራውያን፣ ፉታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፣ ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ከእነዚህ የመጡ ጐሣዎች ነበሩ።

54. የሰልሞን ዘሮች፤ቤተ ልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኵሌታ፣ ጾርዓውያን።

55. በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።