ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሌሎቹ የይሁዳ ጐሣዎች

1. የይሁዳ ዘሮች፤ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል።

2. የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤት ደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዚህም የጾርዓውያን ጐሣዎች ናቸው።

3. የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።

4. ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።

5. የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።

6. ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።

7. የሔላ ወንዶች ልጆች፤ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው።

8. የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።

9. ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።

10. ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፤ ከሥቃይና ከጒዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

11. የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ።

12. ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒር ናሐሽን ከተሞች የቈረቈረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።

13. የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ጎቶንያል፣ ሠራያ።የጎቶንያል ወንዶች ልጆች፤ሐታት፣ መዖኖታይ።

14. መዖኖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ።ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።

15. የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም።የኤላ ልጅ፤ቄኔዝ።

16. የይሃሌልኤል ወንዶች ልጆች፤ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣ አሣርኤል።

17. የዕዝራ ወንዶች ልጆች፤ዬቴር፣ ሜሬድ፣ ዔፌር፣ ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች አንዲቱ ማርያምን፣ ሸማይንና የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደች።

18. አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የሦኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች፤ እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።

19. የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።

20. የሺሞን ወንዶች ልጆች፤አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።

21. የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣

22. ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።

23. ሰዎቹ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።

ስምዖን

24. የስምዖን ዘሮች፤ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፤

25. ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው።

26. የማስማዕ ዘሮችልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዘኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።

27. ሰሜኢ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ ጐሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።

28. የኖሩባቸውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤ ቤርሳቤህ፣ ሞላደ፣ ሐጻርሹዓል፣

29. ቢልሃ፣ ዔጼም፣ ቶላድ፣

30. ቤቱኤል፣ ሔርማ፣ ጺቅላግ፣

31. ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሱሲም፣ ቤት ቢሪ፣ ሽዓራይም፤ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው።

32. በአካባቢያቸው የሚገኙት መንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ አምስት ከተሞች ናቸው፤

33. በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ እስከ በኣል የሚዘልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን፣ የትውልድ መዝገብም አላቸው።

34. ሞሾባብ፣ የምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያስ፣

35. ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ ልጅ፣ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ

36. እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆባ፣ የሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓዲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣

37. የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ፤

38. እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጐሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ የየቤተ ሰባቸውም ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤

39. እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተ ምሥራቅ እስካለው እስከ ጌደር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።

40. በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው።

41. እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።

42. ከእነዚሁ አምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኰረብታማ አገር ወረሩ።

43. አምልጠው የቀሩትን አማሌቃውያን ፈጅተው እስከ ዛሬ በዚያው ይኖራሉ።