ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የራባ ከተማ መያዝ

1. ነገሥታት ለጦርነት በሚሄዱበት በጸደይ ወራት፣ ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ ወደ ራባትም ሄዶ ከበባት፤ ዳዊት ግን ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር። ኢዮአብም ራባትን ወግቶ አፈራረሳት፤

2. ዳዊት የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ነበረ፤ ይህንንም በዳዊት ራስ ላይ ጫኑለት፤ እንዲሁም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።

3. በዚያ የነበረውንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው። ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረጉ። ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

ከፍልስጥኤማውያን ጋር የተደረገ ጦርነት

4. ከዚያም በኋላ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በጌዝር ጦርነት ተደረገ፤ በዚያ ጊዜ ኩሳታዊው ሴቦካይ የራፋይም ዘር የሆነውን ሲፋይን ገደለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ድል ተመቱ።

5. ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ፤ የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጌት ተወላጅ የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።

6. ደግሞም ጌት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ ይህም እንደዚሁ ከራፋይም ዘር ነበረ።

7. እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።

8. በጌት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በሰዎቹ እጅ ወደቁ።