ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36
  37. 37
  38. 38
  39. 39
  40. 40

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ፣ ይለቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው።

2. እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

3. ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤሎሂም) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም።

4. በእንግድነት የሚኖሩባትን የከነዓንን ምድር እንድሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።

5. ደግሞም በግብፃውያን ሥር በባርነት ሆነው ያሰሙትን የእስራኤላውያንን የሥቃይ ድምፄ ሰምቻለሁ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ።

6. “ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ።

7. “የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ (ኤሎሂም) እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኔንም ታውቃላችሁ።

8. ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

9. ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላዳመጡትም።

10. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

11. “ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን እስራኤላውያን ከአገሩ እንዲወጡ ይፈቅድላቸው ዘንድ ንገረው።”

12. ሙሴ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ “እስራኤላውያን ያልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል፤ እኔ ለራሴ ተብታባ ሰው ነኝ” አለው።

የሙሴና የአሮን የትውልድ መዝገብ

13. በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብፅ እንዲያወጡ አዘዛቸው።

14. የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ፣ እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው።

15. የስምዖን ወንዶች ልጆች፣ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና የከነዓናዊቷም ልጅ ሳኡል ነበሩ። እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው።

16. በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው፤ ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።

17. የጌድሶን ወንዶች ልጆች በትውልዳቸው ሎቤኒና ሰሜኢ ነበሩ።

18. የቀዓት ወንዶች ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፤ ቀዓት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ።

19. የሜራሪ ወንዶች ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ነገዶች እነዚህ ናቸው።

20. እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።

21. የይስዓር ወንዶች ልጆች፣ ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ።

22. የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፣ ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ።

23. አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

24. የቆሬ ወንዶች ልጆች፣ አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፤ እነዚህ የቆሬ ነገድ ጐሣ ናቸው።

25. የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት፤ እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ።

26. እግዚአብሔር (ያህዌ) “እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ አውጡ” ብሎ የነገራቸው እነዚህኑ አሮንንና ሙሴን ነበር።

27. ስለ እስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት፣ የግብፅን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ነበሩ።

28. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን በግብፅ በተናገረው ጊዜ፣

29. እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ የነገርሁህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው።”

30. ሙሴ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ፈርዖን ምን ብሎ ይሰማኛል? አንደበቴ ኮልታፋ ነው።”