ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሙሴ መሞት

1. ሙሴ ከሞአብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ፣ ወደ ናባው ተራራ ወጣ። በዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ምድሪቱን ሁሉ አሳየው፤ ይኸውም ከገለዓድ እስከ ዳን፣

2. ንፍታሌምን ሁሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት፣ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ፣

3. ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ ነው።

4. ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፣ ለዘሮቻችሁ እሰጣለሁ’ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር ይህች ናት። በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም” አለው።

5. እግዚአብሔር (ያህዌ) እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር (ያህዌ) አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ።

6. በሞዓብ ምድር በቤተ ፌጎር ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ ቀበረው፤ ይሁን እንጂ መቃብሩ የት እንደሆነ እስከ ዛሬ ማንም አያውቅም።

7. ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ዓመት ነበር፤ ሆኖም ዐይኑ አልፈዘዘም፤ ጒልበቱም አልደከመም።

8. የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት።

9. ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ነበርና፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን አደመጡት፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረጉ።

10. እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም።

11. እግዚአብሔር (ያህዌ) ልኮት፣ እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብፅ በፈርዖን፣ በሹማምቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም።

12. ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኀይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስፈሪ ተግባር የፈጸመ ማንም ሰው የለም።