ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከነዓንን መሰለል

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

2. “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።”

3. ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤

4. ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፤

5. ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፤

6. ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፤

7. ከይሳኮር ነገድ፣ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፤

8. ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፤

9. ከብንያም ነገድ፣ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤

10. ከዛብሎን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤

11. ከምናሴ ነገድ ይህም የዮሴፍ ነገድነው፤ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤

12. ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤

13. ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤

14. ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፤

15. ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል።

16. እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።

17. ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ነጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ።

18. ምድሪቱ ምን እንደምትመስልና የሚኖሩባትም ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፣ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች መሆናቸውን እዩ።

19. የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ?

20. ዐፈሩስ እንዴት ያለ ነው? ለም ወይስ ደረቅ? ደናም ወይስ ደን አልባ? በተቻለ መጠን ከምድሪቱ ፍሬ ይዛችሁ ኑ። ወቅቱ የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር።

21. ስለዚህ ወጥተው ከጺን ምድረ በዳ አንሥቶ በሌቦ ሐማት በኩል እስከ ረአብ ድረስ ዘልቀው ምድሪቱን አጠኑ።

22. በኔጌብ በኩል አልፈው አኪመን፣ ሴሲና ተላሚ የተባሉ የዔናቅ ዝርያዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን መጡ። ኬብሮን የተመሠረተችው ጣኔዎስ በግብፅ ምድር ከመቈርቈሯ ሰባት ዓመት አስቀድሞ ነበር።

23. ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ይህንንም ከሮማንና ከበለስ ጋር በመሎጊያ አድርገው ለሁለት ተሸከሙት።

24. እስራኤላውያን የወይን ዘለላ ስለ ቈረጡባትም ያች ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተባለች።

25. ምድሪቱንም አሥሠው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ።

ሰላዮቹ ያቀረቡት የአሠሣ ውጤት

26. ሰዎቹም፣ ሙሴና አሮን መላውም የእስራኤላውያን ማኅብረ ሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረ በዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ ተመለሱ፤ ያዩትንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ አስረዱ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።

27. ለሙሴም እንዲህ ብለው ነገሩት፤ “ወደ ላክኸን ምድር ዘልቀን ገባን፤ ማርና ወተት የምታፈስስ ናት፤ ፍሬዋም ይኸው።

28. በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ግን ኀያላን ሲሆኑ፣ ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፤ እንዲያውም የዔናቅን ዝርያዎች በዚያ አይተናል።

29. አማሌቃውያን የሚኖሩት በኔጌብ፣ ኬጢያውያን ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በኰረብታማው አገር፣ ከነዓናውያን የሚኖሩት ደግሞ በባሕሩ አቅራቢያና በዮርዳኖስ ዳርቻ ነው።”

30. ከዚያም ካሌብ ሕዝቡን በሙሴ ፊት ጸጥ አሰኝቶ፣ “እንውሓ! ምድራቸውን እንውረስ፤ ማሸነፍም እንችላለን” አላቸው።

31. ከእነርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን፣ “ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ፣ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሉ።

32. እነዚህም ስለ ሰለሏት ምድር በእስራኤላውያን መካከል እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አሠራጩ፤ “ያየናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ግዙፎች ናቸው፤

33. ኔፊሊምንም በዚያ አይተናል፤ የዔናቅ ዝርያዎች የመጡት ከኔፊሊም ነው። ራሳችንን ስናየው እንደ አንበጣ ነበርን፤ በእነርሱ ዐይን የታየነውም በዚሁ መልክ ነበር።