ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28
  29. 29
  30. 30
  31. 31
  32. 32
  33. 33
  34. 34
  35. 35
  36. 36

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሁለተኛው የሕዝብ ቈጠራ

1. ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤

2. “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከየቤተ ሰቡ ቊጠሩ።”

3. ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤

4. “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤

5. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤በፈለስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤

6. በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤

7. እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

8. የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣

9. የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።

10. ሁለት መቶ አምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከእርሱ ጋር ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤

11. የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም።

12. የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤

13. በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤

14. እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።

15. የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤

16. በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤

17. በአሮዲ በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤

18. እነዚህ የጋድ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከነዚህ የተቈጠሩት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

19. ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል።

20. የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤

21. የፋሬስ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በኤስሮም በኩል፣ የኤስሮማውያን ጐሣ፤በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጐሣ፤

22. እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

23. የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣በፋዋ በኩል፣ የፋዋውያን ጐሣ፣

24. በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤

25. እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።

26. የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤

27. እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

28. የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

29. የምናሴ ዘሮች፤በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤

30. የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣

31. በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣

32. በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣በኦፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣

33. የኦፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ።

34. እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።

35. የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤

36. የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በዔዴን በኩል፣ የዔዴውናውያን ጐሣ፤

37. እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።

38. የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣

39. በሶፋን በኩል፣ የሶፋናውያን ጐሣ፣በሑፋም በኩል፣ የሑፋማውያን ጐሣ፤

40. የቤላ ዘሮች በአርድና በናዕማን በኩል፤በአርድ በኩል፣ የአርዳውያን ጐሣ፣በናዕማን በኩል፣ የናዕማናውያን ጐሣ፤

41. እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።

42. የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች።እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣

43. ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ሥልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

44. የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በዩምና በኩል፣ የዩምናውያን ጐሣ፣በየሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤

45. እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ።

46. አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው።

47. እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

48. የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣

49. በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ፤

50. እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

51. ባጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።

52. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

53. “ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ።

54. በርከት ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቊጥር መሠረት ይረከባል።

55. የመሬት ድል ድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።

56. እያንዳንዱም ርስት በትል ልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።

57. በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጐሣ፣በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤

58. እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤የሊብናውያን ጐሣ፣የኬብሮናውያን ጐሣ፣የሞሖላውያን ጐሣ፣የሙሳውያን ጐሣ፣የቆሬያውያን ጐሣ።ቀዓት የእንበረም ቅድመ አያት ነበር፤

59. ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብፅ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች።

60. አሮንም የናዳብና የአብዮድ፣ የአልዓዛርና የኢታምር አባት ነበር።

61. ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ።

62. አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺህ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ አብረዋቸው አልተቈጠሩም።

63. ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ካለው ከሞዓብ ሜዳ ላይ የእስራኤልን ሕዝብ በቈጠሩበት ወቅት የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው።

64. ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤

65. ምክንያቱም በእርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነግሮአቸው ነበር፣ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።