ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 5:11-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ፈጽመው ከድተውኛል፤”ይላል እግዚአብሔር።

12. በእግዚአብሔር ላይ ሐሰትን ተናገሩ፤እንዲህም አሉ፤ “እሱ ምንም አያደርግም!ክፉ ነገር አይደርስብንም፤ሰይፍም ራብም አናይም፤

13. ነቢያቱ ነፋስ እንጂ ሌላ ነገር አይደሉም፤ቃሉም በውስጣቸው የለም፤ያሉት ሁሉ በእነርሱ ላይ ይመለስ።”

14. ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሕዝቡ ይህን ቃል ስለ ተናገረ፣ቃሌን በአፍህ ውስጥ የሚፋጅ እሳት፣ይህንም ሕዝብ ማገዶ አደርጋለሁ፤እሳቱም ይበላቸዋል።

15. የእስራኤል ቤት ሆይ፣” ይላል እግዚአብሔር፤“ከሩቅ ሕዝብን አመጣባችኋለሁ፤ጥንታዊና ብርቱ፣ቋንቋውን የማታውቁት፣ ንግግሩንምየማትረዱት ሕዝብ ነው።

16. የፍላጻቸው ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው።

17. ሰብልህንና ምግብህን ጠራርገው ይበሉብሃል፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይውጣሉ፣በጎችህንና ከብቶችህን ይፈጃሉ፤የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ያወድማሉ፤የታመንህባቸውንም የተመሸጉ ከተሞች፣በሰይፍ ያጠፉአቸዋል።

18. “ይሁን እንጂ፣ በዚያን ዘመን እንኳ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈጽሜ አላጠፋችሁም።

19. ሕዝቡ፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ሁሉ ነገር ለምን አደረገብን?’ ብለው ቢጠይቁ ‘እኔን፣ እንደ ተዋችሁኝና በራሳችሁ ምድር ባዕዳን አማልክትን እንዳገለገላችሁ፣ እንደዚሁ የእናንተ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።

20. “በያዕቆብ ቤት ይህን አሰሙ፣በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤

21. እናንት ዐይን እያላችሁ የማታዩ፣ጆሮ እያላችሁ የማትሰሙ፣ሞኞችና የማታስተውሉ ሰዎች ይህን ስሙ፤

22. ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤“በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን?ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።

23. ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልከኛ ልብ አለው፤መንገድ ለቆ ሄዶአል፤

24. በልባቸውም፣‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።

25. በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል።ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሎአችኋል።

26. “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።

27. ወፎች እንደሞሉት ጐጆ፣ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤

28. ወፍረዋል፤ ሰብተዋልም።ክፋታቸው ገደብ የለውም፤ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙአልቆሙላቸውም፤ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።

29. ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?”ይላል እግዚአብሔር።እንዲህ ዐይነቶቹን ሕዝብ፣እኔ ራሴ ልበቀላቸው አይገባኝምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 5