ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 13:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

9. “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የይሁዳን ትዕቢትና የኢየሩሳሌምን እብሪት እንደዚሁ አጠፋለሁ።

10. ቃሌን መስማት እምቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ።

11. መቀነት በሰው ወገብ ላይ እንደሚታሰር፣ መላው የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር ተጣብቆ ለስሜ ምስጋናና ክብር፣ የኔ ሕዝብ እንዲሆንልኝ አድርጌው ነበር፤ ሕዝቤ ግን አልሰማም’ ይላል እግዚአብሔር።

12. “እንዲህ በላቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል” ይላል። እነርሱም፣ “ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ አናውቅምን?” ቢሉህ፣

13. እንዲህ በላቸው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናትን፣ ነቢያትን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሁሉ ጨምሮ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።’ ”

14. አንዱን ሰው ከሌላው ጋር፣ አባትንና ወንድ ልጅን እርስ በእርስ አጋጫለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ያለ ሐዘኔታ፣ ያለ ምሕረትና ያለ ርኅራኄ አጠፋቸዋለሁ።’ ”

15. እግዚአብሔር ተናግሮአልና፣ስሙ፤ ልብ በሉ፤ትዕቢተኛም አትሁኑ።

16. ጨለማን ሳያመጣ፣በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።

17. ባትሰሙ ግን፣ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኮአልና፣ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።

18. ለንጉሡና ለእናቱ ለእቴጌዪቱ፣የክብር ዘውዳችሁ፣ከራሳችሁ ይወድቃልና፣ከዙፋናችሁ ውረዱ” በላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 13