ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 12:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጒዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው።የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?

2. አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰደዋል፤አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል።ሁል ጊዜ አንተ በአፋቸው ላይ አለህ፤ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

3. ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እኔን ታውቀኛለህ፤ ታየኛለህ፤ስለ አንተም ያለኝን ሐሳብ ትመረምራለህ።እንደሚታረዱ በጎች ንዳቸው፤ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው፤

4. ምድሪቱ በዝናብ እጦት የምትጐዳው፣የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው?ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ደግሞም ሕዝቡ፣“በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።

5. “ከእግረኞች ጋር ሮጠህ፣እነርሱ ካደከሙህ፣ከፈረሰኞች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ?በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 12