ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 61:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድ፣ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ከእነርሱም ጋር የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

9. ዘሮቻቸው በመንግሥታት፣ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ፤የሚያዩአቸውም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የባረካቸው ሕዝብ እንደሆኑ ያውቃሉ።

10. በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ሙሽራዪቱም በዕንቆቿ እንደምታጌጥ፣የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።

11. ምድር ቡቃያ እንደምታበቅል፣የተክል ቦታ ችግኝ እንደሚያፈላ፣ጌታ እግዚአብሔርም በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ጽድቅንና ምስጋናን ያበቅላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 61