ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አብድዩ 1:3-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥየምትኖር፣መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ለራስህም፣“ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?” የምትል፣የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

4. እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ከዚያ አወርድሃለሁ”ይላል እግዚአብሔር።

5. “ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ዘራፊዎችም በሌሊት ቢገቡ፣የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለምን?ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ጥቂት ቃርሚያ አይተዉምን?አንተ ግን ምንኛ ጥፋት ይጠብቅሃል!

6. ዔሳው ግን እንዴት ተዘረፈ?የሸሸገውስ ሀብት ምንኛ ተመዘበረ!

7. ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ድንበር ይገፉሃል፤ጓደኞችህ ያታልሉሃል፤ ያሸንፉህማል፤እንጀራህን የበሉ ወጥመድ ይዘረጉብሃል፤አንተ ግን አታውቀውም።

8. “በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?”ይላል እግዚአብሔር።

9. ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ተገድሎ ይጠፋል።

10. በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፣በዕፍረት ትሸፈናለህ፤ለዘላለምም ትጠፋለህ።

11. እንግዶች ሀብቱን ዘርፈው ሲሄዱ፣ባዕዳንም በበሮቹ ሲገቡ፣በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ ሲጣጣሉ፣በዚያ ቀን ገለልተኛ ሆነህ ተመለከትህ፣አንተም ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆንህ።

12. ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፤በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤በጭንቀታቸውም ቀን፣በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።

13. በጥፋታቸው ቀን፣በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤በጥፋታቸው ቀን፣በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤በጥፋታቸው ቀን፣ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር።

14. ስደተኞቻቸውን ለመግደል፣በመንታ መንገድ መጠባበቅ አይገባህም ነበር፣በጭንቀታቸው ቀን፣የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።

15. “በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሶአል፤አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አብድዩ 1