ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 16:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ወልደአዴር የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀበለ፤ የጦር አዛዦቹንም በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ። እነርሱ ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤልማ ይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ግምጃ ቤት ከተሞች ሁሉ ድል አድርገው ያዙ።

5. ባኦስ ይህን በሰማ ጊዜ ራማን መገንባቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ።

6. ንጉሥ አሳም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ አመጣቸው፤ እነርሱም ባኦስ ይሠራበት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ወሰዱ፤ አሳም ጌባንና ምጽጳን ሠራባት።

7. በዚያን ጊዜም ባለ ራእዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ሳይሆን በሶርያ ንጉሥ ስለ ታመንህ፣ የሶርያ ንጉሥ ሰራዊት ከእጅህ አምልጦአል።

8. ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ቊጥር ካላቸው ሠረገላዎቻቸውና ፈረሶቻቸው ጋር ኀያል ሰራዊት አልነበሩምን? ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጠህ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 16