ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዳንኤል 9:24-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. “ዐመፃን ለማስቆም፣ ኀጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና፣ እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል።

25. “ይህንን ዕወቅ፤ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣ ሰባት ሱባዔና ሥልሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል። ኢየሩሳሌም ከጐዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋር ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።

26. ከሥልሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም፣ ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን ይደመስሳል። ፍጻሜውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጆአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዳንኤል 9