ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፍጥረት 17:21-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይስሐቅ ጋር አደርጋለሁ።”

22. እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ላይ ወጣ።

23. በዚያችም ዕለት አብርሃም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትንና ከውጭ በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች በሙሉ ገረዛቸው።

24. አብርሃም ሲገረዝ ዕድሜው 99 ዓመት ነበር።

25. ልጁም እስማኤል ሲገረዝ 13 ዓመቱ ነበር።

26. አብርሃምና ልጁ እስማኤል፣ ሁለቱም በዚያኑ ቀን ተገረዙ።

27. በአብርሃም ቤት ያሉ ወንዶች ሁሉ፣ በቤቱ የተወለዱትም ሆኑ ከውጭ በገንዘብ የተገዙ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፍጥረት 17