ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘፀአት 6:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ (ኤሎሂም) እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኔንም ታውቃላችሁ።

8. ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

9. ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላዳመጡትም።

10. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

11. “ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን እስራኤላውያን ከአገሩ እንዲወጡ ይፈቅድላቸው ዘንድ ንገረው።”

12. ሙሴ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ “እስራኤላውያን ያልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል፤ እኔ ለራሴ ተብታባ ሰው ነኝ” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘፀአት 6