ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 7:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ለምስጋና የሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ እንጂ አንዳች አይደር።

16. “ ‘መሥዋዕቱ ስእለት በመፈጸሙ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ ከሆነ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ የተረፈውም ሁሉ በማግስቱ ይበላ።

17. እስከ ሦስት ቀን የቆየ ማንኛውም የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቃጠል።

18. ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኵስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 7