ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕዝራ 4:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. አገረ ገዡ ሬሁምና ጸሓፊው ሲምሳይ በኢየሩሳሌም ላይ ለንጉሡ ለአርጤክስስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉ፤

9. ደብዳቤው የተጻፈው፣ ከአገረ ገዡ ሬሁም፣ ከጸሓፊው ሲምሳይ በትሪፖሊስ፣ በፋርስ፣ በአርክ፣ በባቢሎን፣ እንዲሁም በሱሳ ማለትም በኤላማውያን ላይ ዳኞችና ገዦች ከሆኑት ከተባባሪዎቻቸው፣

10. ደግሞም ታላቁና ኀያሉ አስናፈር አፍልሶ በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ሌሎች ሕዝቦች ነው።

11. የላኩለት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ለንጉሥ አርጤክስስ፣በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚኖሩት አገልጋዮችህ የተላከ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕዝራ 4