ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕዝራ 1:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ቂሮስ የፋርስ ንጉሥ በሆነ በመጀመሪያው ዓመት፣ እግዚአብሔር የቂሮስን መንፈስ አነሣሥቶ በመንግሥቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም በጽሑፍ እንዲሰፍር አደረገ፤ ይህ የሆነው በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

2. “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ የሚለው ይህ ነው፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ ምድር በምትገኘው በኢየሩሳሌምም ለእርሱ ቤተ መቅደስ እንድሠራ አዞኛል።

3. ከሕዝቡ መካከል በእናንተ ዘንድ የሚኖር ማናቸውም ሰው አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና በዚያ ለሚኖረው አምላክ፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ይሥራ፤

4. ባሉበት ስፍራ የሚቀሩ በየትኛውም አገር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስጦታ እንዲሆን በበጎ ፈቃድ ከሚያቀርቡት መባ በተጨማሪ ብርና ወርቅ፣ ዕቃና እንስሳ በመስጠት ይርዷቸው።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕዝራ 1