ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 5:23-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልከኛ ልብ አለው፤መንገድ ለቆ ሄዶአል፤

24. በልባቸውም፣‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።

25. በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል።ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሎአችኋል።

26. “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።

27. ወፎች እንደሞሉት ጐጆ፣ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤

28. ወፍረዋል፤ ሰብተዋልም።ክፋታቸው ገደብ የለውም፤ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙአልቆሙላቸውም፤ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።

29. ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?”ይላል እግዚአብሔር።እንዲህ ዐይነቶቹን ሕዝብ፣እኔ ራሴ ልበቀላቸው አይገባኝምን?

30. “የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር፣በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤

31. ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወዳሉ፤ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 5