ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 49:31-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. “ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።

32. ግመሎቻቸው ይዘረፋሉ፤ከብቶቻቸውንም አንጋግተው ይነዱባቸዋል፤ጠጒሩን የሚቀነብበውን ወገንእበትናለሁ ከየአቅጣጫው መዓትይላል እግዚአብሔር፤

33. “ሐጾር የቀበሮዎች መፈንጫ፣ለዘላለም ባድማ ትሆናለች፤ማንም በዚያ አይኖርም፤የሚቀመጥባትም አይገኝም።”

34. በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

35. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ የኀያልነቷን መሠረት፣የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።

36. ከአራቱ የሰማይ ማእዘናት፣በኤላም ላይ አራቱን ነፋሳት አመጣለሁ፤ወደ አራቱም ነፋሳት እበትናቸዋለሁ፤ከኤላም የሚማረኩት የማይደርሱበት፣አገር አይገኝም።

37. ነፍሳቸውን በሚሹ ጠላቶቻቸው ፊት፣ኤላምን አርበደብዳለሁ፤በላያቸው ላይ መዓትን፣ይኸውም ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“ፈጽሜ አስካጠፋቸውም ድረስ፣በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

38. ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

39. “ነገር ግን የኋላ ኋላ፣የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 49