ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 13:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ለንጉሡና ለእናቱ ለእቴጌዪቱ፣የክብር ዘውዳችሁ፣ከራሳችሁ ይወድቃልና፣ከዙፋናችሁ ውረዱ” በላቸው።

19. በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፤የሚከፍታቸውም አይኖርም፤ይሁዳ ሁሉ ተማርኮ ይሄዳል፤ሙሉ በሙሉም ይዘጋል።

20. ዐይኖቻችሁን ከፍታችሁ፣ከሰሜን የሚመጡትን እዩ።ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣የተመካሽባቸው በጎች የት አሉ?

21. ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽያስተማርሻቸው፣ባለ ሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ?እንደምትወልድ ሴት፣ምጥ አይዝሽምን?

22. “ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽራስሽን ብትጠይቂ፣ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 13