ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 34:28-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤የመከረኞችን ጩኽት ሰማ።

29. እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል?እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤

30. ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።

31. “ሰው ለእግዚአብሔር እንዲህ ቢል፣ የተሻለ ነበር፤‘እኔ በደለኛ ነኝ፤ ከእንግዲህ ግን አልበድልም፤

32. ማየት ያልቻልሁትን አስተምረኝ፤ኀጢአት ሠርቼ እንደሆነም፣ ደግሜ አልሠራም።’

33. ታዲያ አንተ ለመናዘዝ ፈቃደኛ ሳትሆን፤እግዚአብሔር እንደ ወደድህ ይከፍልሃልን?መወሰን ያለብህ አንተ ነህ እንጂ፣ እኔ አይደለሁም፤እንግዲህ የምታውቀውን ንገረኝ።

34. “አስተዋዮች ይናገራሉ፤የሚሰሙኝም ጠቢባን እንዲህ ይሉኛል፤

35. ‘ኢዮብ ያለ ዕውቀት ይናገራል፤ቃሉም ማስተዋል ይጐድለዋል።’

36. ምነው ኢዮብ እስከ መጨረሻ በተፈተነ ኖሮ!እንደ ክፉ ሰው መልሶአልና፤

37. በኀጢአቱም ላይ ዐመፅን ጨምሮአል፤በመካከላችን ሆኖ በንቀት አጨብጭቦአል፤በእግዚአብሔርም ላይ ብዙ ተናግሮአል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 34