ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 61:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ለድኾች የምሥራች እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛል።ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ለምርኮኞች ነጻነትን፣ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል፤

2. የተወደደውን የእግዚአብሔርን ዓመት፣የአምላካችንንም የበቀል ቀን እንዳውጅ፣የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤

3. በጽዮን ያዘኑትን እንዳረጋጋ፣በዐመድ ፈንታ፣የውበት አክሊል እንድደፋላቸው፣በልቅሶ ፈንታ፣የደስታ ዘይት በራሳቸው ላይ እንዳፈስላቸው፣በትካዜ መንፈስ ፈንታ፣የምስጋና መጐናጸፊያ እንድደርብላቸው ልኮኛል፤እነርሱም የክብሩ መግለጫ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር የተከላቸው፣የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።

4. የጥንት ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤በቀድሞ ጊዜ የወደሙትን መልሰው ያቆማሉ፤ከብዙ ትውልድ በፊት የወደሙትንፍርስራሽ ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።

5. መጻተኞች የበግ መንጎቻችሁን ያግዳሉ፤ባዕዳን በዕርሻችሁና በወይን ተክል ቦታችሁ ላይ ይሠሩላችኋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 61