ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 58:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም፣ ‘አለሁልህ’ ይልሃል።“የጭቈና ቀንበር፣የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ፣

10. ለተራበው ብትራራለት፣የተገፉት እንዲጠግቡ ብታደርግ፣ብርሃንህ በጨለማ ያበራል፤ሌሊትህም እንደ ቀትር ፀሓይ ይሆናል።

11. እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ይመራሃል፤ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ዐጥንትህን ያበረታል፤በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ።

12. ወገኖችህ የቀድሞ ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤የጥንቱንም መሠረት ያቆማሉ፤አንተም፣ የተናዱ ቅጥሮችን አዳሽ፣ባለ አውራ መንገድ ከተሞችን ጠጋኝ ትባላለህ።

13. “እግሮችህ ሰንበትን እንዳይሽሩ ብታሳርፍ፣በተቀደሰው ቀኔ የልብህን ባታደርግ፣ሰንበትን ደስታ፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን የተከበረ ብለህ ብትጠራው፣በገዛ መንገድህ ከመሄድ፣እንደ ፈቃድህ ከማድረግና ከከንቱ ንግግር ብትቈጠብ፣

14. በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤በምድር ከፍታዎች ላይ እንድትጋልብ፣የአባትህን የያዕቆብን ርስት ጠግበህ እንድትበላ አደርግሃለሁ” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 58