ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 57:5-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በባሉጥ ዛፎች መካከል፣ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሥር በዝሙት የምትቃጠሉ፣በሸለቆዎች፣ በዐለት ስንጣቂዎችም ውስጥልጆቻችሁን የምትሠዉ አይደላችሁምን?

6. በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮችውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቊርባን አፍስሰሻል፤የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን?

7. ዐልጋሽን ከፍ ባለውና በረጅሙ ኰረብታ ላይ አነጠፍሽ፤በዚያም መሥዋዕትሽን ልታቀርቢ ወጣሽ።

8. ከመዝጊያሽና ከመቃንሽ ጀርባ፣የጣዖት ምስሎችሽን ሰቀልሽ፤እኔን ትተሽ መኝታሽን ገላለጥሽ፤በላይም ወጥተሽ በጣም ገለጥሽው፤መኝታቸውን ከወደድሽላቸው ጋር ስምምነት አደረግሽ፤ዕርቃናቸውንም አየሽ።

9. የወይራ ዘይት ይዘሽ፣ሽቶ በላዩ ጨምረሽ ወደ ሞሎክ ሄድሽ፤መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ አገር ላክሽ፤እስከ ራሱ እስከ ሲኦልም ዘለቅሽ።

10. በመንገድ ብዛት ደከምሽ፤ነገር ግን ‘ተስፋ የለውም’ አላልሽም፤የጒልበት መታደስ አገኘሽ፤ስለዚህም አልዛልሽም።

11. “እኔን የዋሸሽኝ፤ማንን ፈርተሽ፣ ማንንስ ሠግተሽ ነው?እኔን ያላስታወስሽው፣ይህንንም በልብሽ ያላኖርሽው፣እኔን ያልፈራሽው፣ዝም ስላልሁ አይደለምን?

12. ጽድቅሽንና ሥራሽን አጋልጣለሁ፤እነርሱም አይጠቅሙሽም።

13. ለርዳታ በምትጮኺበት ጊዜ፣የሰበሰብሻቸው ጣዖቶች እስቲ ያድኑሽ!ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ሽውሽውታም ይበትናቸዋል።እኔን መጠጊያው ያደረገ ሰው ግን፣ምድሪቱን ይወርሳል፤የተቀደሰ ተራራዬንም ገንዘቡ ያደርገዋል።”

14. እንዲህ ይባላል፤“አብጁ፤ አብጁ፤ መንገድ አዘጋጁ፤ከሕዝቤ መንገድ ዕንቅፋት አስወግዱ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 57