ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 53:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመቶ፣ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

9. በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣አሟሟቱ ከክፉዎች፣መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ።

10. መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

11. ከነፍሱ ሥቃይ በኋላ፣የሕይወት ብርሃን ያያል፤ ደስም ይለዋል፤ጻድቅ ባሪያዬ በዕውቀቱ ብዙዎቹን ያጸድቃል፤መተላለፋቸውንም ይሸከማል።

12. ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋር እሰጠዋለሁ፤ምርኮውን ከኀያላን ጋር ይካፈላል፤እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ከክፉ አድራጊዎችም ጋር በመቈጠሩ፣የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 53