ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 5:10-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።

11. የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋማልደው ለሚነሡ፣እስኪያነዳቸውም ወይን በመጠጣትሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸ

12. በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።

13. ስለዚህ ሕዝቤዕውቀት በማጣቱ ይማረካል፤መኳንንቱም በራብ ይሞታሉ፤ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።

14. ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፣አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋርወደዚያ ይወርዳሉ።

15. ሰው ይዋረዳል፤የሰው ልጅም ዝቅ ዝቅ ይላል፤የእብሪተኛውም ዐይን ይሰበራል።

16. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።

17. በጎችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደሚሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤የበግ ጠቦቶችም በባለጠጎች ፍርስራሽ ላይ ሣር ይበላሉ።

18. ኀጢአትን በማታለል ገመድ ለሚስቡ፣በደልንም በሠረገላ ማሰሪያ ለሚጐትቱ ወዮላቸው!

19. በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኵል፤ሥራውንም ያፋጥን፤የእስራኤልን ቅዱስ፣ የእርሱን ዕቅድእንድናውቃት ትቅረብ፤ትምጣም ለሚሉ ወዮላቸው!”

20. ክፉውን መልካም፣መልካሙን ክፉ ለሚሉብርሃኑን ጨለማ፣ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ጣፋጩን መራራ፣መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!

21. ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፣በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!

22. የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፣የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!

23. ጒቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፣ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 5