ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 5:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ወዳጄ፣ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ወዳጄ በለምለም ኰረብታ ላይየወይን ቦታ ነበረው።

2. መሬቱን ቈፈረ፤ ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት።በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤የወይን መጭመቂያ ጒድጓድም አበጀ፤ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።

3. “እናንት በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስቲ ፍረዱ።

4. ከዚህ ካደረግሁለት በላይ ለወይኔ ቦታ ምንሊደረግለት ይገባ ነበር?መልካም የወይን ፍሬ ያፈራል ብዬስጠብቅ ለምን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ?

5. እንግዲህ በወይኔ ቦታምን እንደማደርግ ልንገራችሁ፤ዐጥሩን እነቅላለሁ፤ለጥፋት ይጋለጣል፤ግንቡንም አፈርሳለሁ፣መረጋገጫም ይሆናል።

6. የማይኰተኰትና የማይታረምጠፍ መሬት አደርገዋለሁ፤ኵርንችትና እሾኽም ይበቅልበታል፤ዝናብም እንዳይዘንብበትደመናዎችን አዝዛለሁ።”

7. የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርየወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤የይሁዳ ሰዎችምየደስታው አትክልት ናቸው።ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።

8. ስፍራ ለሌሎች እስከማይተርፍ፣ቤትን በቤት ላይ በመጨመር፣መሬትን ከመሬት ጋር በማያያዝ፣ለብቻችሁ በምድር ተስፋፍታችሁ ለምትኖሩ ወዮላችሁ

9. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤“ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፣የሚያማምሩም ቤቶች ኗሪ ያጣሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 5