ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 48:10-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እነሆ፤ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ፤በመከራ እቶን ፈትኜሃለሁ።

11. ስለ ራሴ፣ ስለ ራሴ ስል አደርጋለሁ፤ራሴን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ?ክብሬን ለማንም አልሰጥም።

12. “ያዕቆብ ሆይ፤የጠራሁህ እስራኤል ሆይ፤ ስማኝ፤እኔ እኔው ነኝ፤ፊተኛው እኔ ነኝ፤ ኋለኛውም እኔ ነኝ።

13. ምድርን የመሠረተች የእኔው እጅ ናት፤ሰማያትን የዘረጋችም ቀኝ እጄ ናት፤በምጠራቸው ጊዜ፣ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ።

14. “ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አድምጡም፤ከጣዖቶች አስቀድሞ እነዚህን የተናገረ ማን ነው? የእግዚአብሔር ምርጥ ወዳጅ የሆነ፣እርሱ በባቢሎን ላይ ያቀደውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፤ክንዱም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።

15. እኔ፣ እኔው ራሴ ተናግሬአለሁ፤በርግጥ እኔ ጠርቼዋለሁ፤አመጣዋለሁ፤ሥራውም ይከናወንለታል።

16. “ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤“ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።”አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱልከውኛል።

17. የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣የሚበጅህ ምን እንደሆነ የማስተምርህ፣መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።

18. ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።

19. ዘርህ እንደ አሸዋ፣ልጆችህ ስፍር እንደሌለው ትቢያ በሆኑ ነበር፤ስማቸው አይወገድም፤ከፊቴም አይጠፋም።

20. ከባቢሎን ውጡ፣ከባቢሎናውያንም ሽሹ!ይህን በእልልታ አስታውቁ፤ ዐውጁት፤እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተናገሩ፤“እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብንተቤዥቶታል” በሉ።

21. በምድረ በዳ ሲመራቸው አልተጠሙም ነበር፤ውሃ ከዐለት አፈለቀላቸው፤ዐለቱን ሰነጠቀ፤ውሃውም በኀይል ፈልቆ ወጣ።

22. “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 48