ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 47:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ተብለሽ አትጠሪም።

2. ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ፤መሸፋፈኛሽን አውልቂ፤ቀሚስሽንም ከፍ ከፍ አድርጊ፤ ባትሽን ግለጪ፤እየተንገዳገድሽ ወንዙን ተሻገሪ።

3. ዕርቃንሽ ይገለጥ፤ኀፍረትሽ ይታይ፤እበቀላለሁ፤እኔ ማንንም አልተውም።

4. የሚቤዠን የእስራኤል ቅዱስ፣ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

5. “አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት፣ተብለሽ አትጠሪም።

6. ሕዝቤን ተቈጥቼ ነበር፤ርስቴን አርክሼው ነበር፤አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኋቸው፤አንቺ ግን አልራራሽላቸውም፤በዕድሜ በገፉት ላይ እንኳ፣እጅግ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 47