ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 30:20-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ጌታ የጭንቀት እንጀራና የመከራ ውሃ ቢሰጥህም፣ አስተማሪህ ከእንግዲህ አይሰወርብህም፤ ዐይኖችህም አስተማሪህን ያያሉ።

21. ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።

22. ከዚያም በብር የተለበጡትን ጣዖቶችህንና በወርቅ የተለበዱ ምስሎችህን ታዋርዳለህ፤ “ከዚህ ወግ” ብለህም እንደ መርገም ጨርቅ ትጥላቸዋለህ።

23. በምድርም ለዘራኸው ዘር ዝናብን ይሰጥሃል፤ ከመሬትም የሚገኘው ፍሬ ምርጥና የተትረፈረፈ ይሆናል። በዚያን ቀን ከብቶችህ በትልቅ ሜዳ ላይ ይሰማራሉ።

24. የዕርሻ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በላይዳ የተለየውን ገፈራና ድርቆሽ ይበላሉ።

25. በታላቁ የዕልቂት ቀን ምሽጎች ሲፈርሱ፣ በረጅም ተራራ ሁሉና ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ላይ ወራጅ ወንዝ ይፈስሳል።

26. እግዚአብሔር የሕዝቡን ስብራት ሲጠግን፣ ያቈሰለውንም ሲፈውስ፣ ጨረቃ እንደ ፀሓይ ታበራለች፤ የፀሓይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት ዕጥፍ ይደምቃል።

27. እነሆ፤ የእግዚአብሔር ስም፣ከሚነድ ቍጣ፣ ጥቅጥቅ ካለና ከሚትጐለጐል የጢስ ደመና ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ከንፈሮቹ ቍጣን የተሞሉ ናቸው፤ምላሱም የሚባላ እሳት ነው።

28. እስትንፋሱ እንደሚጠራርግ፣እስከ ዐንገት እንደሚደርስም የውሃ ሙላት ነው፤መንግሥታትን በጥፋት ወንፊት ያበጥራቸዋል፤በሕዝቦችም መንጋጋ፣መንገድ የሚያስት ልጓም ያስገባል።

29. በሌሊት የተቀደሰ በዓል ስታከብሩእንደምትዘምሩ፣ትዘምራላችሁ፤ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ እስራኤል ዐለት፣ሰዎች ዋሽንት እየነፉ በደስታ እንደሚወጡ፣የእናንተም ልብ እንዲሁ ሐሤት ያደርጋል።

30. እግዚአብሔር በሚነድ ቍጣና በሚባላ እሳት፣በወጀብና በነጐድጓድ፣ በበረዶም ድንጋይ፣ግርማ የተሞላበትን ድምፁን ሰዎች እንዲሰሙ አድርጎ ያሰማል፤ክንዱም ስትወርድ ያሳያቸዋል።

31. የእግዚአብሔር ድምፅ አሦርን ያስደነግጣል፤በትሩም ይመታቸዋል።

32. እግዚአብሔር የሚያወርድባቸው የቅጣትበትር ሁሉ፣በከበሮና በበገና ድምፅ የታጀበ ነው፤በጦርነትም ክንዱን አሳይቶ መታቸው።

33. ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያስፍራ ተዘጋጅቶአል፤ለንጉሡም ተበጅቶአል፤ማንደጃ ጒድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስእንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 30