ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 22:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እግዚአብሔር የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርበራእይ ሸለቆ፣የመጯጯኺያ የመረገጥና የሽብር፣ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።

6. ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ቂርም ጋሻዋን አነገበች

7. መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል፤

8. የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል።በዚያን ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤

9. የዳዊት ከተማ፣ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤በታችኛውም ኵሬ፣ውሃ አጠራቀማችሁ።

10. በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።

11. ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከ ታችሁም፤ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።

12. በዚያን ቀን ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣ጠጒራችሁን እንድትነጩማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።

13. ነገር ግን እነሆ፤ ተድላና ደስታ፣ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ፤“እንብላ እንጠጣነገ እንሞታለንና” አላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 22