ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 11:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።

2. የእግዚአብሔር መንፈስ፣የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኀይል መንፈስ፣የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

3. እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።

4. ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።

5. ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 11